GetTransfer.com ምንድን ነው?
GetTransfer.com በግል ለሚደረጉ ጉዞዎች ተሳፋሪዎችን እና አሽከርካሪዎችን የሚያገናኝ ዓለም አቀፍ የሆነ የመስመር ላይ (የኦንላይን) የገበያ ቦታ ነው። በ GetTransfer.com ላይ የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች የጉዞዎች እና የመላኪያ አገልግሎት ጥያቄዎችን ማቅረብ፣ እና ከትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢዎች ግብዣዎችን መቀበል ይችላሉ። እነዚህ ግብዣዎች የተሽከርካሪው ትክክለኛ ፎቶዎችን፣ በተጠቃሚ የተሰጡ የተሸከርካሪ ደረጃን እና የተጠናቀቁ ጉዞዎችን ያካትታሉ፣ ሁሉም ተጠቃሚው ክፍያ ከመፈጸሙ በፊት የሚገኙ ናቸው።
አዘውትሮ የሚጠየቁ ጥያቄዎች
በሰዓት የመኪና ኪራይ ምን ያህል ነው?
በሰዓት ሹፌር ያለው መኪና መከራየት ይችላሉ፡፡
ለምሳሌ ብዙ የሥራ ጉዞ ቀጠሮዎች የሚኖርዎ ከሆነ ወይም በአስጎብኚ ለሚታገዝ ጉብኝት ወይም በራስዎ መንገድ ለመጓዝ ተስማሚ አማራጭ፡፡
በማዘዣ ቅፅዎ ላይ በሚገኘው የአስተያየት መስጫ ላይ የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ቀን/ጊዜ በመምረጥ ለአሽከርካሪው ስለ ጉዞው ዝርዝር መረጃ ይስጡ፡፡
የጉዞዎን ዝርዝር በሚመለከት ጥሩ እና የበለጠ ትክክለኛ ዋጋ ያላቸውን የአገልግሎት አቅርቦቶችን ለማግኘት፣ እባክዎ ማንኛውንም ተያያዥነት ያለው መረጃ ያካትቱ፡ መንገድ ላይ የሚገኙ መቆሚያዎች፣ ቦታ እና ጊዜያቸው፣ የተሽከርካሪ እና አሽከርካሪ ምርጫ፡፡
የማድረስ አገልግሎት እንዴት ማዘዝ ይቻላል?
የማድረስ አገልግሎትን ለማዘዝ፣ እባክህ የማድረሻ ቀኑን፣ የመነሻ እና የመዳረሻ ቦታዎችን፣ ልኬቶች እና ይዘቶችን (ለምሳሌ 10 ኪ.ግ የሚመዝን ሻንጣ፣ እቅፍ አበባዎች) ግለፅ፡፡
በተቻለ ፍጥነት እንዴት ራይድ ማዘዝ ይቻላል?
በተጨማሪም ወዲያውኑ ወይም በተቻለ ፍጥነት ራይድ ከፈለጉ ማዘዝ ይችላሉ፡፡ በቅርበት የሚገኘውን የአገልግሎት አቅርቦት ለመምረጥ እንዲረዳዎ አሽከርካሪው እስኪደርስ ድረስ ያለውን ጊዜ ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
በዋጋው ላይ የተካተቱ ነገሮች ምንድን ናቸው?
አሽከርካሪዎች ለአገልግሎት ጥያቄዎ የራሳቸውን ዋጋ ነው የሚያቀርቡት፡፡ የአሽከርካሪው ዋጋ ነፃ የመጠበቂያ ጊዜ (በአየር ማረፊያ፣ በባህር ወይም በወንዝ የተጓዥ ወደብ ተርሚናሎች 60 ደቂቃ፣ በባቡር ጣቢያዎች 30 ደቂቃ እና በሁሉም ሌሎች ቦታዎች 15 ደቂቃ)፣ የነዳጅ እና የመንገድ ክፍያዎች ካሉ እነሱንም ያካትታል፡፡
አሽከርካሪው ሳይደርስ ቢቀርስ?
በመጀመሪያ፣ አሽከርካሪዎን ለማግኘት ይሞክሩ፡፡ የአሽከርካሪው የመገኛ ዝርዝሮች በግል መለያዎ ውስጥ በሚገኘው የጉዞ ዝርዝር ላይ ተገልፀዋል፡፡ አሽከርካሪውን በስልክ ወይም በአጭር መልእክት ለማግኘት ካልቻሉ፣ እባክዎ ሁኔታውን ለድጋፍ ቡድን ያሳውቁ፡፡
የ GetTransfer.comን አሽከርካሪዎች ማመን እችላለሁ?
የአገልግሎታችን ደንበኞች የአሽከርካሪዎችን አፈፃፀም ይገመግማሉ፡፡ የተጠቃሚዎችን ግብረ መልስ በመተንተን ኮንትራቱን የገባው ሰው ምንም የአፈፃፀም ችግር ያልተመዘገበበት ከሆነ ብቻ አብረን መስራት እንቀጥላለን፡፡
ደንበኞቻችን ሁልጊዜ ጥሩውን እንዲመርጡ የማጓጓዝ አገልግሎት ሰጪው የሚያቀርባቸው አገልግሎቶች ዋጋዎችንም ይጨምራሉ፡፡
በረራዬ ቢዘገይስ?
በአየር ማረፊያዎች ነፃ የመጠበቂያ ጊዜ 60 ደቂቃ ነው፡፡ መዘግየቱ ከአንድ ሰዓት በላይ የሚወስድ ከሆነ እባክዎ የድጋፍ ቡድናችንን ያግኙ፡፡
መኪናው ሻንጣዬ መያዝ እንደሚችል እንዴት አረጋግጣለሁ?
የሻንጣዎን ልኬትና ብዛታቸውን በትዕዛዝ ቅፁ የአስተያየት ቦታ ላይ ይግለፁ፡፡ ለምሳሌ ርዝመታቸው 180 ሳ.ሜ የሆነ 2 ስካይ ቦርሳዎች እና ሁለት ሻንጣዎች፡፡ አሽከርካሪዎች መስፈርቶችዎን በማየት ላቀረቡት ጥያቄ ተስማሚ የሆነ ተሸከርካሪ ካላቸው አሽከርካሪዎች የአገልግሎት አቅርቦት ይደርስዎታል፡፡ አሁንም እርግጠኛ ካልሆኑ፣ እባክዎ የድጋፍ ቡድናችንን ያግኙ፡፡